በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚሰማሩ የፖሊስ አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡

ተለጥፏል 2020-10-26
Card image

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚሰማሩ የፖሊስ አባላት ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡


"የትምህርት ተቋማትን ሰላም ማስጠበቅ" በሚል ርዕስ የሰላም ሚኒስቴር ከፌዴራል ፓሊስ፣ ከኢትዮጵያ ፓሊስ ዩንቨርሲቲ ኮሌጅ እና ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተዘጋጀና ለሁለት ቀናት የሚቆይ ስልጠና በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚሰማሩ የፖሊስ አባላት በሰንዳፋ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ እየተሰጠ ይገኛል፡፡


መድረኩን በንግግር የከፈቱት በሰላም ሚኒስቴር የህግ ማስከበር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ፍሬአለም ሽባባው በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተዘግተው የነበሩትን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መልሶ ለማስጀመር የፓሊስ አባላት ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል።


ወ/ሮ ፍሬአለም በሽታው እየተስፋፋ ከመሆኑም አኳያ ጥንቃቄ ማድረግ እና ግጭቶች እንዳይከሰቱ የሰራዊት አባላት ጠንክረው በመስራት የመማር ማስተማሩን ሂደት ሰላማዊ እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።


የፓሊስ አባላት ጸጥታ ማስከበር ብቻ ሳይሆን የሚፈጠሩ ስህተቶችን ወደ ትምህርት በመቀየር መካሪም አስተማሪም እንዲሆኑ ክብርት ሚኒስትር ዴኤታዋ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።

ፎቶዎች


ዜና

Card image
2020-11-01
ማስታወቂያ
Card image
2020-10-23
በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ የተላለፈ መልዕክት
Card image
2020-10-22
ለአገር ውስጥ የምርምር ጆርናል አሳታሚዎች እና አዘጋጆች የምርምር ጆርናል እውቅና ለማግኘት እንድታመለክቱ ስለመጋበዝ
Card image
2020-10-08
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ እርቀ ሰላም ኮሚሽን ጋር በጋራ ሊሰሯቸው በሚችሏቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር አደረገ፡፡
Card image
2020-10-06
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የ2013 በጀት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት እቅድ ክንውንን አስመልክቶ የተዘጋጀ ጋዜጣዊ መግለጫ
Card image
2020-10-06
በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት በትምህርትና ሥልጠና ተቋማት ውስጥ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራን ለመምራት የሚያስችል መመሪያ መዘጋጀቱ ተገለፀ፡፡