ዜናዎች

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የዳዉሮ ተርጫ ካምፓስ ተመረቀ

ተለጥፏል 2020-10-31
Card image

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ የዳዉሮ ተርጫ ካምፓስ ተመረቀ

ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ ሶስተኛ ካምፓስ የሆነዉ የዳዉሮ ተርጫ ካምፓስ የሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ፣የሚኒስቴር መስሪቤቱ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣የደቡብ ብሔር ብሔረሰብና ህዝቦች የክልል የተለያዩ አመራሮች፣የወላታ እና ዳዉሮ ዞን ዋና አስተዳዳሪዎችና ሌሎች አመራሮችና የህብረተሰብ ክፍሎች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ተመርቋል፡፡

በምርቃት ሥነስርዓቱ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት ክቡር ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ መንግስት የህብረተሰባችንን የልማት ጥያቄዎች አቅም በፈቀደ መልኩ ከመቸዉም ጊዜ በበለጠ በፍታሐዊነት ተደራሽ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ትምህርት፣ምርምር እና ሳይንሳዊ ባህሎችን እያጎለበትን መሄድ ሀገራችን ለምታደርገዉ የዕድገትና የብልጽግና ጉዞ የማይተካ ሚና ስላላቸዉ ዩኒቨርስቲዎቻችን ይህንኑ በዉል በመገንዘብ በትጋት መተግበር እንዳለባቸዉ ሚኒስትሩ አብራርተዋል፡፡

ለፍትሐዊነትና ተደራሽነት የትምህርት ተቋማትን በምናስፋፋበት ወቅት ተቋሞቻችን ለትምህርት ጥራትም ከፍተኛ ጥንቃቄ በማድረግ መስራት እንደሚያስፈልግ ሚኒስትሩ አክለዋል፡፡

የዳዉሮ ዞን ዋና ከተማ የሆነችዉ ተርጫ ከተማ ከወላይታ ሶዶ 170 ኪ.ሜ በላይ ርቃ የምትገኝ ስትሆን በዚህ ርቀት የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርስቲ በዳዉሮ ዞን ተጨማሪ ካምፓስ መክፈቱ የሁለቱን ዞኖች ህዝቦች በጋራ የመልማት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ላይ ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለዉ የገለፁት ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ሌሎች አከባቢዎችም ከዚህ መማር አለባቸዉ ብለዋል፡፡

ፎቶዎች


ዜና

Card image
2021-06-11
በህደሴ ግድብ ግንባታ ዓለም አቀፍ የውሃ ህጎች ላይ የሚመክር ጉባኤ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ትናንት ተጀመረ
Card image
2021-06-11
ከ350 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የመጀመሪያዉ ምዕራፍ ግንባታዉ የተጠናቀቀዉ የቦረና ዩኒቨርሲቲ ተመረቀ
Card image
2021-06-10
ሰባት የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ማሰልጠኛ የልህቀት ማእከላት በ150 ሚሊየን ዶላር እየተገነቡ ነዉ
Card image
2021-06-10
"ድምጻችን ለ''ነጻነታችንና ሉዓላዊነታችን " በሚል መሪ ቃል የዩኒቨርስቲዎች ተማሪዎች ድምጻቸዉን አሰሙ
Card image
2021-06-03
“የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ምሁራን የአገራችን ሉዓላዊነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ምሁራዊ ሚናቸዉን ከመቼዉም ጊዜ በላይ በጋራ በመቆም ሊወጡ ይገባል”
Card image
2021-06-03
በደቡብ ክልል የሚገኙ ዘጠኝ ዩኚቨርስቲዎች 3ኛውን የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር አካሄዱ ፡፡ የወላይታ ሶዶ ዩኚቨርስቲ ማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል የእናቶችና ህጻናት ሀክምና ማዕከልም ዛሬ ተመርቋል፡፡