ለመንግስት ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ
በኮቪድ-19 ምክንያት ተቋርጦ የነበረውን ትምህርት ለማስቀጠል ዩኒቨርሲቲዎች ከጥቅምት 23/2013 ዓ.ም. ጀምሮ ተማሪዎቻቸው ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ማስተላለፋቸው ይታወቃል፡፡
አሁን በተፈጠረው ወቅታዊ ሁኔታ ምክንያት የተማሪዎችን እንቅስቃሴ ለተወሰነ ጊዜ መግታት አስፈልጓል፡፡ በዚሁ መሠረት፡-
1. እስካሁን ወደ ዩኒቨርሲቲዎቻችሁ የደረሳችሁ ተማሪዎች በግቢያችሁ እንድትቆዩና ከተቋሞቻችሁ ኃላፊዎች የሚሰጣችሁን ማሳሰቢያ እየተከታተላችሁ እንድትንቀሳቀሱ፤ በአካባቢያችሁ የሚታዩ ማንኛውንም የተለየ ጉዳይ ለተቋሞቻችሁ ኃላፊዎች እንድታሳውቁ፤
2. በጉዞ ላይ ያላችሁ ወደ ወላጆቻችሁ አከባቢ ወይም ወደ ተቋማችሁ ከሁለቱ ወደ ቀረበው ቦታ ደርሳችሁ እንድትቆዩ፤
3. እስከ አሁን ከወላጆቻችሁ አካባቢ ያልተነሳችሁና ጉዞ ያልጀመራችሁ በቀጣይ ተለዋጭ ማስታወቂያ እስኪወጣ ድረስ ባላችሁበት እንድትቆዩ፤
4. ሁሉም ተቋማት በቂ ጥበቃ እንዲደረግላቸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ጋር እየሰራ መሆኑን ተገንዝባችሁ ተረጋግታችሁ እንድትቆዩ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡
5. መረጃዎችን በየወቅቱ የምንሰጥ መሆኑን እየገለጽን ማናቸውንም ማስታወቂያም ሆነ መረጃ ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ወይም ከዩኒቨርሲቲያችሁ ፕሬዝደንት ብቻ እንድትከታተሉ እናሳስባለን፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 0118332789