News

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የ2013 ክረምት በጎ ፈቃድ ስራ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የአቅመ ደካሞችን ቤቶች በማደስ ጀመረ

Posted 2021-07-07
Card image

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የ2013 ክረምት በጎ ፈቃድ ስራ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የአቅመ ደካሞችን ቤቶች በማደስ ጀመረ፡፡


የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ፤ ከኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርስቲ እና የተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በመገኘት የአቅመ ደካሞችን ቤቶች የማደስ ፕሮግራም አስጀምረዋል፡፡


የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሩ ክቡር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ ይህ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡት የማህበረሰብ አገልግሎት አንዱ አካል መሆኑን ገልጸዉ የአቅመ ደካሞችን ቤት ለማደስ በአጋርነት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 


የዚህ ፕሮግራም ዋና አላማም የበጎ-ፈቃድ አገልግሎት ለማስጀመርና በክፍለ ከተማዉ የተመረጡ አቅመ ደካሞችን ቤት ለማደስ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ እነዚህ ቤቶችም በአጭር ጊዜ ዉስጥ የሚገነቡ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ 


የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ፕ/ሮ ጣሰዉ ወልደ ሃና በበኩላቸዉ ዩንቨርስቲያቸዉ በርካታ የማህበረሰብ አገልግሎት በአዲስ አበባና ከአዲስ አበባ ዉጪ እየሰሩ መሆናቸዉን ገልጸዉ ይህም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡


የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል ረዲ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርና መሰል ተቋማት በዚህ ተግባር ላይ በባለቤትነት መሳተፋቸው ክረምቱን ተከትሎ ለችግር የሚዳረጉ በርካታ አቅመ ደካሞች ያግዛል ብለዋል።


ቤታቸዉ የሚታደስላቸዉ እናቶች በበኩላቸዉ ክረምቱ ለዝናብና ለተለያዩ በሽታዎች ተጋላጭ እንዳደረጋቸዉ ገልጸዉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የቤቶች እደሳ ለማድረግ በማስጀመሩ የተሰማቸዉን ደስታ ገልጸዋል።


በፕሮግራሙ ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ፤ ሚኒስትር ዴኤታዎች ክቡር ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌና ክቡር ፕ/ር አፈወርቅ ካሱ፤በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስራአስኪያጅ ጥራቱ በየነን ጨምሮ በአዲስ አበባ የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎችና ተጠሪ ተቋማት ፕሬዝዳንቶችና ዳይሬክተሮች እንዲሁም በቂርቆስ ክፍለ ከተማ የአካባቢ ማህበረሰብ ተገኝቷል፡፡

Pictures


News

Card image
2021-07-09
Registration Criteria for Individual Researchers
Card image
2021-05-25
2012 E.C Top 100 Students Based on Entrance(Grade 12) Exam Result
Card image
2021-05-25
2012 E.C Top 100 Female Students Based on Entrance(Grade 12) Exam Result
Card image
2021-05-08
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር የተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያ ቅጽ 2013 ዓ.ም
Card image
2021-04-30
H.E. Dr. Samuel Urkato visited Misale Driver training academy
Card image
2021-04-14
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ ፕሮግራሞች ዝርዝር