News

የፈጠራና የምርምር ስራዎችን ለማበረታታትና ትስስር ለመፍጠር የሚያስችል ኮንቬንሽን ሊካሄድ ነዉ

Posted 2021-07-08
Card image

የፈጠራና የምርምር ስራዎችን ለማበረታታትና ትስስር ለመፍጠር የሚያስችል ኮንቬንሽን ሊካሄድ ነዉ


የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የፈጠራና የምርምር ስራዎችን ለማበረታታት፣ እዉቅና ለመስጠትና ትስስር ለመፍጠር የመጀመሪያ የሆነዉን የከፍተኛ ትምህርት ምርምርና ቴክኖሎጂ ኮንቬንሽን ከሃምሌ 5-8 2013ዓ.ም በአዲስ አበባ እያዘጋጀ ነዉ፡፡

ዝግጅቱን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ፕሮፌሰር ጽጌ ገብረማሪያም የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ ፕሬዝዳንትና የፕሮፌሰሮች ካዉንስል ሰብሳቢ፣ ዶ/ር አባተ ጌታሁን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ አማካሪ እና ዶ/ር ሰለሞን መኮንን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክተር ጀኔራል ናቸዉ፡፡

ፕሮፌሰር ጽጌ ገብረማሪያም በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ምርምር፣ ቴክኖሎጂና የኢንዱስትሪ ትስስር ኮንቬንሽን ከሃምሌ 5-8 /2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡

በነዚህ ቀናትም ስድስት የፓናል ዉይይቶች የሚካሄዱ ሲሆን የመጀመሪያዉ የሰዉ ሃይል፣ ሳይንስ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽንና የ10 አመት መሪ እቅድ ተስፋዎችና ተግዳሮቶች፤ ሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ፈጠራ ለዘላቂ ልማት ከአለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊና ከብሄራዊ አንጻር ፤ የአፍሪካ ህብረት ዲፕሎማሲ፣ የሰላምና ደህንነት አሁናዊ ሁኔታ፤ የዲጅታል ስትራቴጂ ቴክኖሎጂ ትምህርትና ምርምር ለአስተዳደር በዩንቨርስቲዎቻችንና በሙያ ማሰልጠኛዎቻችን ያለዉ ሚና፤የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት የሙያ ስልጠና ለማጠናከር ከኢንደስትሪ ጋር የማስተሳሰር ሂደት ተስፋና ተግዳሮት እንዲሁም በኢትዮጲያ ትምህርትና ስልጠና ምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግር ጥራትና አግባብነት ላይ ያተኮሩ ዉይይቶች ይካሄዳሉ ብለዋል፡፡

በዝግጅቱ ዘጠኝ ዓይነት ተቋማት እንደሚሳተፋ የገለጹት ዶ/ር አባተ ጌታሁን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ አማካሪ ሲሆኑ 57 የመንግስትና የግል ዩንቨርስቲዎችና የምርምርና ቴክኖሎጂ ተቋማት፣ 51 የቴክኒክና ሙያ ተቋማት፣ አንጋፋና ወጣት ሳይንቲስቶች፣ የኢንዱስትሪ መሪዎች፣ ከፍተኛ ባለሃብቶችና ኢንቨስተሮች፣ የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎች፣ የባንክና ኢንሹራንስ መሪዎች፣ ታዋቂ አገር በቀል እዉቀት አቃቢዎችና ፖሊሲ አዉጪዎች ተሳታፊ ይሆናሉ በአንድ ተገናኝዉም እዉቀትና ቴክኖሎጂ ይገበያያሉ ብለዋል፡፡

ዶ/ር ሰለሞን መኮንን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠን ዳይሬክተር ጀኔራል ኮንቬንሽኑ “ወደ እዉቀት መር ኢኮኖሚ” በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ መሆኑንና በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ገልጸዋል፡፡ በሃገራችን ባሉ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ችግር ፈቺ የሆኑ ምርምሮች ይሰራሉ፡፡ የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ይፈጠራሉ ነገር ግን ወደ ተግባር ገብተዉ ለሃገራችን ጎላ ሚና ከመስጠት አንጻር ፋይዳቸዉ በጣም ዝቅተኛ ነዉ ብለዋል፡፡

በመሆኑም ይህን ኮንቬንሽን ሊያዩት የሚመጡ ተሳታፊዎች ለራሳቸዉ ጥቅም እንዲያዉሉት ትስስርና ትብብር ለመፍጠር፤ እንዲሁም ጥሩ ስራ የሰሩ የመንግስትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ ተማሪዎችና መምህራን እዉቅና ለመስጠት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በዝግጅቱ መጨረሻም የአጋርነት ስምምነትና እዉቅና የሚሰጥ መሆኑንና ዝግጅቱም በየአመቱ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል፡፡

Pictures


News

Card image
2021-07-09
Registration Criteria for Individual Researchers
Card image
2021-05-25
2012 E.C Top 100 Students Based on Entrance(Grade 12) Exam Result
Card image
2021-05-25
2012 E.C Top 100 Female Students Based on Entrance(Grade 12) Exam Result
Card image
2021-05-08
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር የተፈታኞች ቅሬታ ማቅረቢያ ቅጽ 2013 ዓ.ም
Card image
2021-04-30
H.E. Dr. Samuel Urkato visited Misale Driver training academy
Card image
2021-04-14
በኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ ፕሮግራሞች ዝርዝር