ስለ እኛ

የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር, በአዋጅ ቁጥር 1097/2018 እ.ኤ.አ. ጥቅምት 2018 የተቋቋመው የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት እንዲሁም የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና (ቴ/ሙ/ት/ሥ) በኢትዮጵያ እንዲመራ ለማድረግ ነው

በከፍተኛ ትምህርት ተቋሞቻችን የሚኖረን የከፍተኛው እርከን አመራር በተቋማቱ አጠቃላይ አፈፃፀም ላይ የላቀና ጉልህ የሆነ ልዩነት ማስመዘገብ ይችላል፡፡ በመሆኑም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በኩል ልናሳካው ላሰብነው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ግቦቻችን ወሳኝ የሆነውን ይህንን ጉዳይ በጥንቃቄ መፈፀም ይኖርብናል፡፡ በባለፉት ዓመታት የከፍተኛ ትምህርትን ተደራሽነት፣ ጥራት፣ ተገቢነትና ፍትሃዊነትን ለማሻሸል በአመራሩ አማካይነት ያስመዘገብነውን ውጤት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንዲቻልና በከፍተኛው እርከን የሚሰማሩትን ግልፀኝነትና ብቃትን ማዕከል ባደረገ መስፈርት መምረጥ እንደሚገባ ስለታመነበት ከሚመለከታቸው ጋር መግባባት ተፈጥሯል፡፡ይህን ማኑዋል ወደ ሥራ በማስገባት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማትን በብቁ፣ ተወዳዳሪና ውጤታማ ግለሰቦች እንዲመሩ በማድረግ የትምህርት ጥራትና ተገቢነት በማረጋገጥና ተቋማቱ የልህቀት ማዕከል ሆነው ለአገራዊው የሰላም፣ልማትና ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ የበኩላቸውን እንዲወጡ ለማስቻል መስራት ያስፈልጋል፡፡ 

አስተያየት ይስጡ